በፌስቡክ ያግኙን

Click here

If you are not able to use  Amharic font , Please– click Here

ርዕዮት

ብርሃን ወዴት አለ የትስ ነው ጨለማ ?

ግብ ሃገሩ የት ነው የሚያኖር አላማ ?

ምን ሰናይ ወረደ ምን ተአብ ተሰማ ?

መልሱ ከርዕዮት ነው ከራስ ሃሳብ ሸማ

መልሱ ከራዕይ ነው ከነፍስ እንጉርጉሮ ከገዛ ራስ ዜማ

ህዋ ጫፍ እንዲደርስ አድማሱን ተርትሮ

ህልሙን ከአረም ቁልል ጀንበሩን ከግርዶሽ እንዲያወጣ ጭሮ

ነገ ከዚያ በስቲያ ወዲያ በስቲያ ወዲያ እንዲቃኝ አሻግሮ

ርዕዮቱ ጀልባው ነው መርሁ ታንኳው ነው የሚያስጉዘው ታትሮ

ርዕዮቱ አፅሙ ነው የሚያቆመው ማግሮ

ርዕዮት ያላበጀ ያጣ መመልከቻ

እይታ ያልሰራ ሁሉን መፈልፈያ ህቡዕ ምስጢር መፍቻ

መጀመር አያውቅም የለውም ዳርቻ

ባዶ ነው ከንቱ ነው ያለ በስም ብቻ ያለ በአካል ብቻ

የሃሳቡን መነፅር የእምነቱን መነፅር ከአይኑ ያልሰቀለ

ሌትም አልነበረ ቀኑንም አልዋለ

ህያዋን አያውቁት ሙታን መሃል የለ

ወዲህ መነሳሻ ማዶውን መድረሻ

ሁሉን መዳሰሻ ማሽተቻ መቅመሻ

ይፋም አደባባይ መሸሸጊያም ዋሻ

ርዕዮት ነው ጎዳና ርዕዮት ነው ክብሪቱ ህይወት መለኮሻ

ርዕዮት

ቴዎድሮስ ፀጋዬ 2003 .

ትርፋማ መዝናኛ !

 

 
hoto